አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ስድስት ኪሎ አካባቢ ባለቤቱን በጥይት ገደለ

43

አዲስ አበባ  የካቲት 28/2011 አዲስ አበባ ስድስት ኪሎ አካባቢ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል የስራ ባልደረባውና ባለቤቱ የሆነችውን የፖሊስ አባል ዛሬ ረፋድ ላይ በጥይት መግደሉ ተሰማ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ምክትል ሃላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ምትኩ ለኢዜአ እንደገለጹት ተጠርጣሪው የፖሊስ አባል የሆነችውን የትዳር አጋሩን ስድስት ኪሎ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ካምፕ መግደሉን አረጋግጠዋል።

መንስኤው ገና በመጣራት ላይ ቢሆንም ግድያው የተፈፀመው በመካከላቸው በተፈጠረው ጊዜያዊ አለመግባባት መሆኑም ታውቋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም