በተሽከርካሪ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ

56

መቀሌ የካቲት 26/2011 መቀሌ አካባቢ በደረሰው የተሽከርካሪ አደጋ   የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፓሊስ አስታወቀ፡፡

አደጋው የደረሰው ልዩ ስሙ ሀረና ከተባለ ቦታ ድንጋይ ጭኖ ወደ መቀሌ  በመጓዝ ላይ የነበረ ትርቦ ገልባጭ ተሽከርካሪ  60 ሜትር ጥልቀት ባለው  ገደል ውስጥ  በመግባቱ  ነው፡፡

በመቀሌ ከተማ የትራፊክ ጽህፈት ቤት የትራፊክ ድህንነት ቁጥጥርና አደጋ ማጣራት ኃላፊ ኮማንደር ተስፋይ ገብረመድህን ለኢዜአ እንዳሉት ትናንት ምሽት በደረሰው በዚሁ  አደጋ ህይወታቸው ካለፈው  ውጭ ሌላ አንድ ሰው ከባድ የመቁሰል ጉዳት ደርሶበታል፡፡

የመቁሰል ጉዳት የተደረሰበት ሰው በአይደር ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት መሆኑን አመልክተው  የማቾቹ አስክሬን  ቤተሰቦቻቸው እንዲረከቡ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 58211 ኢት ትርቦ ተሽከርካሪ ሾፌር  ጉዳት ሳይደርስበት መትረፉንና በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ሁሉም ተጎጂዎቹ በዚሁ ተሸከርካሪ ላይ ተጭነው የነበሩ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም