ከ4 ሺህ በላይ ተወዳዳሪዎች የተሳተፉበት የቴክኖሎጂ ውድድር አሸናፊዎች በመጪው ሰኞ ይፋ ይደረጋሉ

583

አዲስ አበባ የካቲት 23/2011 ህዋዊ የተሰኘው የቻይና ኩባንያ በኢትዮጵያ ተማሪዎችንና መምህራንን በማሳተፍ ያካሄደው የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ውድድር አሸናፊዎችን በመጪው ሰኞ ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

የቻይናው ቴሌኮምኒኬሽንና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አምራች ኩባንያው ባዘጋጀው በዚህ አገር አቀፍ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር ከ20 ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ ከ4 ሺህ በላይ ተማሪዎች እና መምህራን ተሳትፈዋል።

ውድድሩ ተማሪዎች እና መምህራን በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ያላቸዉን ብቃት ለማሻሻል፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማጠናከርና  የተሻለ ሥርአተ ትምህርት ለማዳበር ያግዛል ተብሏል።

ውድድሩ የተማሪዎችን የወደፊት የቅጥር እድሎች ለማመቻቸት እንደሚያስችልም ተገልጿል።

ህዋዊ ውድድሩን ያዘጋጀው በአዲስ አበባ የቻይና ኤምባሲ፤ ትምህርት ሚኒስቴር እና ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው።