የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ ተመረቀ

128

ደብረ ብርሃን ካቲት 23/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክን በጋራ በይፋ መርቀዋል።

ፓርኩ በ1ሺ100 ሄክታር መሬት ስፋት ላይ የሚያርፍ ሲሆን ፤ ዛሬ ተመርቀው ወደ ስራ የገቡት ስምንት ሼዶች የተገነቡት በ70 ሄክታር ቦታ ላይ ያረፉ ናቸው።

ይሄው በመጀመሪያው የግንባታ ምዕራፍ 72 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት ኢንዱስትሪ ፓርክ ፤ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት እንደሚያመርት ታውቋል።

በቀጣይ የኢንዱስትሪ ፓርክ በግብርና ማቀነባበሪያ ላይ አተኩሮ እንደሚሰራ ከስፍራው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም