ቀዳማዊት እመቤት በአሶሳ ለሚገነባው ትምህርት ቤት የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ

734
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ለሚገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሠረት ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅት

አሶሳ የካቲት 22/2011 ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከልል በአሶሳ ወረዳ ነባር ኮምሽጋ ቀበሌ ለሚገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡

በዚሁ ወቅት ቀዳማዊት እመቤት ባደረጉት ንግግር የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠበት አካባቢ የተመረጠው በቂ የትምህርት  መሠረተ ልማት ስለሌለው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ትምህርት ለሀገር እድገት ዋነኛ መሠረት መሆኑን ያመለከቱት  ቀዳማዊት እመቤት በተለይም የአካባቢው አመራሮች ግንባታው በወቅቱ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ በትኩረት እንዲከታተሉ አደራ ብለዋል፡፡

ትምህርት ቤቱ ለማስገንባት በአካባቢው ተገኝተው መሠረት ድንጋይ በማስቀመጠቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን አዲስ በበኩላቸው  የሚገነባው የትምህርት ተደራሽነት ለማስፋት እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

ትምህርት ቤቱ ተገንብቶ ለአገልግሎት ሲበቃ የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ስያሜ እንደሚኖረው አስታውቀዋል፡፡

ትምህርት  ቤቱ  20 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡