የገቢዎች ሚኒስቴር 14 ቢሊዮን ብር የታክስ ስወራ ያደረጉ 135 ድርጅቶች ላይ እርምጃ መዉሰዱን ገለጸ

68

አዲስ አበባ የካቲት 20/2011 14 ቢሊዮን ብር የታክስ ስወራ ፈጽመዋል ባላቸው 135 ድርጅቶች ላይ እርምጃ መዉሰዱን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

ድርጅቶቹም የጅምላ ነጋዴዎች፣ አከፋፋዮችና የአንደኛ ደረጃ ኮንትራክተሮች መሆናቸዉ ተጠቅሷል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ  የተጠረጠሩበት የታክስ  ደረሰኝ አለመቁረጥና 'ኪሳራ ዉስጥ ነን' በማለት ተመላሽ መጠየቅ መሆናቸዉን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በተወሰደው እርምጃ 105 የየድርጅቶቹ ሰራተኞች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲዉሉ ተደርጎ 64ቱ ፋይላቸዉ ተጣርቶ በፍርድ ቤት ክስ ተመሰርቶባቸዋል።

ሌሎች ድርጅቶች ላይ ከታክስ ስወራ ጋር በተያያዘ ምርመራና ማጣራት እየተደረገባቸው መሆኑም ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም