ጨፌው የስድስት ወራት የጸጥታና ሰላም ስራዎችን በትኩረት ይገመግማል … የክልሉ አፈጉባኤ - ኢዜአ አማርኛ
ጨፌው የስድስት ወራት የጸጥታና ሰላም ስራዎችን በትኩረት ይገመግማል … የክልሉ አፈጉባኤ
86
አዲስ አበባ የካቲት 19/2011 የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ) 5ኛው የስራ ዘመን 4ኛ አመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬና ነገ ይካሄዳል።
በጉባኤው መክፈቻ ላይ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ እንዳሉት፤ ባለፉት 6 ወራት በክልሉ መንግስት የተከናወኑ ተግባራት ይገመገማሉ።
በበጀት አመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ ከተከናወኑት ተግባራት በተለይም በጸጥታና ሰላም ላይ የተሰሩ ስራዎች በዋንኛነት ለውይይት የሚቀርቡ አጀንዳዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ምክር ቤቱ በ8ኛው መደበኛ ጉባኤ ላይ የ2010 ዓ.ም የክልሉ መንግስት የስራ አፈጻጸም በመገምገም አቅጣጫ በማስቀመጥ የ2011 ዓ.ም እቅድ ማውጣቱ ይታወሳል።
ክልሉ ሰላምና ጸጥታን እንዲሁም የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ያስታወሱት አፈ ጉባኤዋ ከአጎራባች ክልሎች ጋር ሰፊ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።
በጉባኤው የሁለት ቀን ውሎ በአስፈጻሚ አካላት የተከናወኑ ስራዎች ይገመገማሉ፣ አዋጆች ይጸድቃሉ፣ ልዩ ልዩ ሹመቶችም ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።