በሰላምና አንድነት ላይ ያተኮረ ውይይት በመቀሌ እየተካሄደ ነው

86

መቀሌ የካቲት 16/2011 በአማራና ትግራይ  አንድነትና ሰላማዊ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ውይይት በመቀሌ እየተካሄደ ነው፡፡

በመቀሌ ዩኒቨርስቲ አስተባባሪነት በተዘጋጀው በዚሁ ህዝባዊ ውይይት ከሁለቱም ክልል እና ከተለያዩ የሃገራችን ዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ ምሁራን፣የኃይማኖት መሪዎችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው፡፡

በዩኒቨርስቲው የህብረተሰብ ቋንቋዎች ኮሌጅ  ዲንና የኮንፈረንሱ አስተባባሪ ዶክተር ገብረእየሱስ ተክሉ ውይይቱ ዛሬ ሲጀመር   እንዳሉት፣የአማራና የትግራይ ህዝቦች አንዱን ከሌላው የሚይለያይና የተሳሰሩ ናቸው፡፡ ፡

ሁለቱም ህዝቦች ከዘመነ ያሬድ ጀምሮው አብረው የኖሩ፣ የትውልድ ሃረጋቸው አንድ እና  በጋብቻ፣በንግድ፣ኢትዮጰያን በመገንባትና አንድነትዋን እንዲጠበቅ ከተለያዩ የውጭ ወራሪ ኃይሎች አብሮው ከተፋለሙት መካከል እንደሚገኙበት ገልጸዋል።

" የአማራና የትግራይ ክልል ህዝቦች ገደብ የለሽ የዘመናት ግንኙነታቸው አንድ እንዲሆኑ አድርጓቿዋል " ያሉት ዶክተር ገብረእየሱስ፣ዛሬ  የውሸት ታሪክ እየተፈበረኩ በመካከላቸው ልዩነት እንዲሰፋ እያደረገ መምጣቱን ተናግረዋል።

"ችግሮቹ ለመፍታትና ለዘመናት የቆየውን ሁለቱን ህዝቦች  የአንድነትና የመልካም ተምሳሌት ግንኙነታቸውን ወደ ነበረበት እንዲመለስ ከልሂቃን/ምሁራን/  ብዙ ይጠበቃል" ብለዋል።

ከመወቃቀስ ይልቅ  ችግሮች በቅንነት በመፈተሽ ለሰላም መንገስ በትጋት መስራት  እንደሚገባም አመልክተዋል።

በውይይቱ " ኢትዮጰያዊነትና ታሪክ" በሚል ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር ዶክተር ስንታየሁ ካሕሳይ የአማራና የትግራይ ህዝቦች አንድነትና ትስስር በታሪክ ሂደት እየጠናከረ የመጣ የዘመናት ክስተት መሆኑን ገልጸዋል።

ሁለቱም ህዝቦች ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን  የሃገርን ሉአላዊነት ከማስከበር፣ከጀግንነትና ከትግል የመጣ ጠንካራ ግንኙነት  እንዳላቸው የገለጹት  ምሁሩ፣" ይህንን መልካም ታሪክ የነበረ፣ያለና የሚኖር ነው" ብለዋል።

"የታሪክ ስህተቶች ካሉ ከስህቶቶቹ ተምሮ ለተሻለ ለውጥ መትጋትና   መማር እንጂ በቀልን ለመውሰድ መሆን የለበትም " ብለዋል፡፡

በማህበረሰቡ ውስጥ የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ በማህበራዊ ሚዲያ በተሳሰተ መልኩ ከሚነዙ ፕሮፖጋንዳዎች መቆጠብ  እንደሚገባ ያመለከቱት ደግሞ ከጂማ ዩኒቨርስቲ የተጋበዙት ዶክተር ደሬሳ ዴቡ ናቸው።

" ተማርን የሚሉ ሰዎችም መስተካከል አለባቸው፣የትናንት ስህተቶች ልንደግም አይገባም፤ የታሪክን ጥቅም ደግሞ ካለፈው ስህተት መማርን ነው" ብለዋል።

የወሎ ዩኒቨርስቲ የሰላምና የግጭት አፈታት ምሁር  አቶ አያናው ሞላ በበኩላቸው፣በሁለቱም ህዝቦች እየሰፉ የመጡትን ጥያቄዎች መመለስ ያለባቸው በመነጋገርና በመወያየት  መሆኑን ተናግረዋል።

በሁሉቱም ህዝቦች ያለውን የመብት ጥያቄ በማዳመጥና ሰጥቶ በመቀበል መርህ ሊመለሱ እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ውይይት የተለያዩ  ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ምክክር እንደሚካሄድባቸውም ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም