የዓይደር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 379 የሕክምና ዶክተሮችን አስመረቀ

54

መቀሌ የካቲት 16/2011 የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ዓይደር የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 379 የሕክምና ዶክተሮችን ዛሬ አስመረቀ።

"በዩኒቨርሲቲው በነበረው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ልጆቻችን ከዓላማቸው ሳይሰተጓጎሉ ለምረቃ በመብቃታቸው ተደስተናል" ሲሉ ወላጆች ገልፀዋል ።

ኮሌጁ ካስመረቃቸው የሕክምና ዶክተሮች መካከል 326ቱ በጠቅላላ ሕክምናና 53ቱ በስፔሻሊስት ኃኪምነት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው።

ከአጠቃላይ ተመራቂዎች መካከልም 97ቱ ሴቶች መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ  በወቅቱ እንደገለፁት ምሩቃን የሀገሪቱን የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ተግባራዊ ከማድረግ ባለፈ ወደ ላቀ ደረጃ የማድረስ ኃላፊነት ተጥሎባችዋል።

ዩኒቨርሲቲው በኮሌጁ አማካኝነት የጤና ሙያተኞችን ከማፍራት ጎን ለጎን በዓይደር ሪፈራል ሆስፒታልና በዓለም አቀፍ የሕክምና ተቋማት ትብብር ለህብረተሰቡ የልብ ቀዶ ሕክምናን ጨምሮ የነፃ የህክምና አገልገሎት አየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል ።

ሆስፒታሉ በዚህ ወር ውስጥ ብቻ ከጀርመንና እስራኤል በመጡ ስፔሻሊስት ኃኪሞች በመታገዝ ከ2 ሺህ በላይ የመስማት ችግር ላለባቸው ወገኖች የህክምና አገልግሎት መስጠቱን ለአብነት ጠቅሰዋል ።

በክብር እንግድነት የተገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤና የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ታገሰ ጫፎ " የህክምና ሙያ የተከበረ ብቻ ሳይሆን ከጤንነትና ደህንነት ጋር የተገናኘ በመሆኑ ተመራቂዎች ህዝቡን በቅንነት ልታገለግሉ ይገባል " ብለዋል ።

ከባህር ዳር ወደ መቀሌ ተጉዘው በልጃቸው ምረቃ ስነ ስርአት ላይ የተገኙት ወይዘሮ ዕፀገነት ወልዴ በበኩላቸው ልጃቸውን ወደ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በሏኳት ወቅት ርቃ በመሄዷ ስጋት አድሮባቸው እንደነበር አስታውሰዋል ።

"በዩኒቨርሲቲው ባለው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ልጄ አንድም ቀን ከትምህርቷ ሳትስተጓጎል ዛሬ ለምረቃ መብቃቷ እጅግ በጣም ተደስቺያለሁ " ብለዋል ።

"በልጄ ምክንያት መቀሌ ከተማ ብዙ ቤተሰብና ዘመዶች አፍርቻለሁ " ሲሉም ተናግረዋል ።

በልጃቸው ምረቃ ስነ ስርአት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከመጡ ቤተሰቦች ጋር  ለመገናኘትና ለመተዋወቅ እንደቻሉ የገለፁት ደግሞ የአዲስ አበባ ነዋሪ አቶ መረሳ አለማየሁ ናቸው።

"ልጄ ከአላማዋ ሳትስተጓጎል ለዚህ ወግ ማዕረግ በመብቃቷ ደሰታ ተሰምቶኛል " ብለዋል ።

በትምህርቷ 3 ነጥብ 84 ውጤት በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቃ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነችው ዶከተር ኪዳን ፍስሃ በቀጣይ የሙያው ሰነ ምግባር በሚጠይቀው መሰረት ህበረተሰቡን በቅንነት ለማገልገል መዘጋጀቷን ገለጿለች ።

ዓይደር የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ማስተማር ከተመሰረተበት ጀምሮ ከ2 ሺህ በላይ የሕክምና ባለሙያዎን ማሰመረቁ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም