የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ የማጠቃለያ ዝግጅቱን በሚሊኒየም አዳራሽ እያቀረበ ነው

73

አዲስ አበባ የካቲት 14/2011 የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ የማጠቃለያ ዝግጅቱን በሚሊኒየም አዳራሽ እያከናወነ ነው።

የኢትዮጵያና ኤርትራ ሕዝቦችን ትስስር ለማጠናከር ያለመና 55 አባላትን የያዘ የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባሕል ቡድን  የካቲት 7 ቀን 2011 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ ይታወቃል።

ቡድኑ ወደ ባሕር ዳር፣ አዳማና ሐዋሳ  በማቅናት የኪነጥበብ ስራዎችን ያቀረበ ሲሆን፤ በሄደባቸው ስፍራዎች ሁሉ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ዛሬ የካቲት 14 ቀን 2011 ዓ.ም ደግሞ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ የተለያዩ የቆዩና ባህልን የሚ9ያንጸባርቁ ጥዑመ ዜማዎችን በማቅረብ የማጠቀለያ መረሃ ግብሩን እያቀረበ ይገኛል። ፡፡

በመዝግጅቱም ምክትል ከንቲባው ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎችና የመዲናይቱ የተለያዩ  የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።

የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ ከሁለት ቀናት በኋላ ወደ ኤርትራ ይመለሳል ተብሎም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ቡድንም ለተመሳሳይ ዓላማና ዝግጅት ከአንድ ወር በኋላ ወደ ኤርትራ እንደሚያቀና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም