ሳዑዲ 850 የህንድ እስረኞችን ልትለቅ ነው

82

የካቲት 14/2011 የሳኡዲ ልዑል መሃመድ ቢል ሳልማን  በህንድ ባደረጉት ጉብኝት ከህንድ አቻቸው ናሬንድራ ሞዲ  አስረኞች እንዲፈቱ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡

የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ልዑሉ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ናሬንድራ ሞዲ  የቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለው 850 የህንድ እስረኞችን እንደሚፈቱ ተናግረዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ሳዑዲ በርካታ ቁጥር ያላቸው የህንድ ዜጎች በእስርቤቶችዋ  ይገኛሉ፡፡

 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር እስከ ጥር 2019 ብቻ በግድያ፣አፈናና እና የተለያዩ አደንዛዥ እፅ እና አልኮል በተያያዘ 2 ሺ 224 ሰዎች መታሰራቸውን ሚኒስቴሩ አክሎ ገልጿል፡፡

2.7 ሚሊዮን የሚሆኑ ህንዳውያንም  በሳዑዲ ዐረቢያ የሚኖሩ ሲሆን በአብዛኛው በኮንስትራክሽን እና አነስተኛ ገቢ በሚያስገኙ ዘርፎች ተሰማርተዋል፡፡

በተመሳሳይ ሳዑዲ አረቢያ ባለፈው ሰኞ 2 ሺ 100 የፓኪስታን እስረኞች እንዲፈቱ ትዕዛዝ ማስተላለፍዋን የፓኪስታን ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር መግለፁን ዘገባው ያመለክታል፡፡

ሳዑዲ አረቢያ ባለፈው ሰኞ ከፓኪስታን የ20 ቢሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ስምምነት የተፈራረመች ሲሆን በተመሳሳይ ከህንድ 100 ቢሊዮን ዶላር በቀጣይ ሁለት ዓመታት የሚተገበር  የኢንቨስመንት ስምምነትም ማድረጋቸውም ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም