የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር 4ኛው የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በመጪው እሁድ ይካሄዳል

66

አዲስ አበባ የካቲት 13/2011 የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በትብብር የሚያዘጋጀው የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር 4ኛው የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል።

''ለደህንነታች እንሩጥ'' በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደውን ውድድር አስመልክቶ አዘጋጆቹ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት፤ ህብረተሰቡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን መከላከል እንዲቻል ግንዛቤ መፈጠር አለበት።

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ገመቺስ ማሞ የውድድሩ ዓላማ ህብረተሰቡ የአካል ብቃት እንስቃሴ የማድረግ ባህሉን በማዳበር ራሱን ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች እንዲካላከል ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል አጋጣሚ እንደሆነ ተናግረዋል።

5 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍነው የጎዳና ላይ ሩጫው መነሻና መድረሻው መገናኛ ዳያስፖራ አደባባይ እንደሆነ ተገልጿል።

100 የሚደርሱ አትሌቶች በውድድሩ የሚሳተፉ ሲሆን 2 ሺህ 500 የሚሆኑ የህክምና ባለሙያዎችና ሌሎች የህብረሰተብ ክፍሎች በሩጫ ውድድሩ ይታደማሉ ተብሏል።

በአትሌቶች መካከል በሚደረገው ውድድር በሁለቱም ጾታ አንደኛ ሆነው ለሚያጠናቅቁ 15 ሺህ ብር፣ ሁለተኛ ለሚወጡ የ10 ሺህ ብር ሶስተኛ ሆነው ለሚያጠቅቁ ደግሞ 7 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከት ተነግሯል።

እንዲሁም ከ4ኛ እስከ 6ኛ ባለው ደረጃ ለሚያጠናቅቁ የገንዘብ ሽልማት እንደሚያገኙ ተጠቁሟል።

ተላላፊ ስላልሆኑ በሽታዎች ያለውን ግንዛቤ ማጎልበት፣ የህክምና ባለሙያዎችና ህብረተሰቡን ማቀራረብ የውድድሩ ዋና ትኩረት ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም