የየመን ተፋላሚ ሃይሎች ጦራቸውን ከወደብ ከተማዋ ሆዳይዳ ለማስወጣት የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ተፈራረሙ

69

የካቲት 11/2011 የየመን መንግሥት እና የሃውቲ ተወካዮች በተባበሩት መንግሥታት አደራዳሪነት የጦር ሃይላቸውን ከወደብ ከተማዋ ለማስወጣት የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት መፈራረማቸው ተነግሯል።

የተባበሩት መንግሥታት ፕሬስ ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው፤ በመጀመሪያው ደረጃ ሃውቲዎች የጦር ሃይላቸውን ከሆዳይዳ፣ ሳሌፍ እና ራስ ኢሳ ያስወጣሉ።

የየመን መንግሥት ሃይልም ከምስራቃዊ ሆዳይዳ እንዲሸሽ ይደረጋል ነው የተባለው።

ተፋላሚ ሃይሎቹ በመርህ ደረጃ ሁለተኛ ዙር ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን ይህም ስምምነት ሙሉ የጦር ሃይላቸውን ከሆዳይዳ ግዛት ሙሉ ለሙሉ ለማስወጣት የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል።

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም