የመቀሌ ሰባ እንደርታ እግር ኳስ ክለብ የባህርዳር አቻውን አሸነፈ

88

መቀሌ የካቲት 10/2011 በኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ የመቀሌ ሰባ  እንደርታ ክለብ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ዛሬ በሜዳው የገጠመው  የባህርዳር አቻውን 1ለ 0 አሸነፈ፡፡

በትግራይ ስቴዲዮም በተካሄደው በዚሁ ጨዋታ የመቀሌ ሰባ  እንደርታ ክለብ የአሸናፊነቱን ጎል ያስቆጠረው በዘጠነኛው ደቂቃ ላይ  በ17 ቁጥሩ ኦሰይ ማውሊ አማካኝነት ነው፡፡

የባህርዳር ተጨዋቾችም ከእረፍት መልስ ተጠናክረው ቢገቡም ግብ  ማስቆጠር አልቻሉም፡፡

መቀሌ ሰባ እንደርታ እግር ኳስ  ክለብ 9 የባህርዳር አቻው ደግሞ 3 የማዕዝን ምቶች ቢያገኙም ወደ ግብ ሊቀይሩ አልቻሉም፡፡

ከውድድሩ ቀደም ብሎ የህወሓት 44ኛው የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በክልሉ አመራሮችና በኪነጥበብ ባለሙያዎች መካከል የእግር ኳስ ውድድር የተካሄደ ሲሆን አመራሮቹ ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸንፈዋል፡፡

በሴት አመራሮችና በኪነጥበብ ባለሙያዎች መካከል በተካሄደው የገመድ ጉተታም የኪነጥበብ ባለሙያዎች አሸናፊ ሆነዋል፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በስቴዲዮሙ ተገኝተው ጨዋታውን ተከታትለዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም