ለህወሓት ምስረታ በዓል የተዘጋጀ የጎዳና ላይ ሩጫ በመቀሌ ከተማ ተካሄደ

60

መቀሌ የካቲት 10/2011 ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የተመሰረተበትን 44ኛው ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በመቀሌ ከተማ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሄደ።

ውድድሩ " የሰማዕታት አደራን ተቀብለን ድህነትና ኋላቀርነትን ለማስወገድ አንድነታችን በማጠናከር እንረባረባለን " በሚል መሪ ሀሳብ ተካሄዷል።

ውድድሩን ያዘጋጁት የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮና ህወሓት ጽህፈት ቤት ናቸው።

የውድድሩ አስተባባሪ አቶ ሶፋኒያስ ከበደ እንደገለፁት መነሻውና መድረሻውን በትግራይ ሰማዕታት ኃውልት ባደረገው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ከ10 ሺህ በላይ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

በውድድሩ ከተሳተፉ ነዋሪዎች መካከል አቶ መሐሪ ገብረእግዚአብሔር " በሀገሪቱ ሰላምና የዲሞክራሲ ስርአት እንዲረጋገጥ ሲሉ ክቡር ህይወታቸውን የከፈሉ ታጋዮችን ለመዘከር በተዘጋጀ ሩጫ በመሳተፌ ደስተኛ ነኝ " ብለዋል ።

"ለሴቶች መብት መከበር ሰማዕት ለሆኑ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ክብር በመሮጤ ደስተኛ ነኝ" ያለችው ደግሞ ወጣት ራሄል አብርሃ ነች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም