ግብርን እንጂ ብድርን ለትውልድ ማውረስ የለብንም - አዳነች አቤቤ

57

አዲስ አበባ የካቲት 10/2011 ህብረተሰቡ ታክስና ግብር የመክፈል ግዴታውን በመወጣት ለመጭው ትውልድ የተሻለች ሀገር እንዲያስረክብ የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ።

ሀገራዊ የታክስና የግብር ንቅናቄን በማስመልከት  'ግዴታዬን እወጣለሁ መብቴን እጠይቃለሁ' በሚል መሪ ሀሳብ ግብር ለሀገሬ የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ተካሄዷል።

ሚኒስትሯ በሩጫው ስነ ስርዓት መክፈቻ ንግግራቸው "ግብርን እንጂ ብድርን ለትውልድ ማውረስ የለብንም" ያሉ ሲሆን ህብረተሰቡ ግብርን በመክፈል ለሀገሩ ያለውን ክብርና ፍቅር ሊገልፅ ይገባል ብለዋል።

ውድድሩ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ግብር በመሰብሰብ፣ ውጤታማ የግብር አሰባሰብ ስርዓት እንዲኖር የሚከናወን የታክሰ ንቅናቄ ነው።

በመክፈቻው ላይ "ግብር ለሀገራችን ክብርና ፍቅር ሲባል የሚከፈልና መልሶ ለራሳችን የሚከፈለን እንጂ ዕዳ ወይም ሸክም አድርገን መውሰድ የለብንም" ሲሉም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

ሩጫው ከ 1 እስከ 10 ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች ከ25 ሺህ እስከ 1 ሺህ 5 መቶ ብር ሽልማት አለው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም