7ኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ቀንን አስመልከቶ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
7ኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ቀንን አስመልከቶ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው
101
አዳማ የካቲት 6/2011 ሰባተኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን ምክንያት በማድረግ በአዳማ ከተማ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው
በዓሉ " ህገ መንግስታዊ ታማኝነታችንና ህዝባዊ ባህሪያችን ጠብቀን የተጀመረው ሀገራዊ ለውጥ እናስቀጥላለን " በሚል መሪ ሃሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ ነገ ይከበራል
በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲዮም የሚከበረው ይሄው ሰባተኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን ምክንያት በማድረግ እየተካሄደ ያለው ውይይት የተመራው በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ለማ መገርሳ ነው፡፡
በፓናል ውይይቱ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን መከላከያ በለው ሂደት ውስጥ የሚል የመነሻ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ታሪካዊ ጉዞ ከትናንት እስከ ዛሬ የሚል የመነሻ ፅሁፍ ደግሞ በአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ብርጋዴል ጀነራል ይልማ መርዳሳ ቀርቧል፡፡
በውይይት መድረኩ የመከላከያ ሚኒስትሯ ወይዘሮ አይሻ መሐመድ፣ አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አርበኞች፡ ሚነስትሮች፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ የአዳማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡