ካርዲናል ብርሃነ እየሱሰ የብሄራዊ ዕርቀ-ሠላም ኮሚሽን ሰብሳቢ ሆነው ተመረጡ

116

አዲስ አበባ  የካቲት5/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ ለኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስን የብሄራዊ ዕርቀ-ሠላም ኮሚሽን ሰብሳቢ አድርገው አገራዊ ሃላፊነት ሰጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህግ ባለሙያዋን የትነበርሽ ንጉሴን ደግሞ  የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ አድርገው ሰይመዋል። 



ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ የብሄራዊ ዕርቀ-ሠላም ኮሚሽን ምክትል ሰብሳቢ አድርገው ከሰየሟቸው
ከወይዘሮ የትነበርሽ ንጉሴ ጋር

መንግስት የኮሚሽኑን ስራ ከመደገፍ ውጭ በስራው ጣልቃ እንደማይገባም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

የኮሚሽኑ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ የስራ ጊዜ ሶስት ዓመት እንደሚሆን ታውቋል። ለግለሰቦቹ የተሰጠው ኃላፊነት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ያላቸውን እውቀትና ልምድ በመጠቀም ሰብሳቢውንና ምክትል ሰብሳቢዋን በሥራ እንዲያገዙ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

ከዚህም ሌላ የሰላም ሚኒስቴር ለኮሚሽኑ ሥራ መቃናት የሚጠበቅበትን ድጋፍ  ያደርጋል ተብሏል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ባካሄደው ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አቅራቢነት ለዕርቀ-ሠላም ኮሚሽን አባልነት የቀረበለትን ሹመቶ ማፅደቁ ይታወሳል።

41 አባላት ያሉተ ኮሚሽኑ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከፖለቲከኞች፣ ከምሁራን፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከአባ ገዳዎች፣ ከታዋቂ ሰዎች እና ከኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የተውጣጡ ናቸው።

ከተለያዩ የሙያና የህይወት መስመር የተጠሩት እነዚህ የኮሚሽኑ አባላት ለጉዳዩ ሁነኛ መፍትሄ ለመስጠት ታልሞ የተመለመሉ መሆናቸውም በዚሁ ወቅት ተገልጿል። 

የብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽንን ለማቋቋም የተዘጋጀው አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር አባላት ወይይት ተደረጎበት የፀደቀው ታህሳስ 16 ቀን 2011 ዓም ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም