ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከተለያዩ አገራት መሪዎች ጋር ተወያዩ

61

አዲስ አበባ  የካቲት 4/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከህብረቱ ጉባዔ ጎን ለጎን ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎችና ከኢስቶኒያ ፕሬዝዳንት ጋር በአህጉራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማርጌሌ፣ ከሞሮኮው ጠቅላይ ሚንስትር ሳአዴዲን ኦቶማን፣ ከአልጄሪያው ጠቅላይ ሚንስቴር አህመድ ኦያህያ እና ከጊኒው ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ ጋርም የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

እንዲሁም ከኢስቶኒያ ፕሬዝዳንት ክርስቲ ካልጁይድ ጋርም መክረዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በትላንትናው ዕለትም ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛና ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በተናጠል የተወያዩ ሲሆን ከአወሮፓ ህብረት ኮሚሽን የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ፌደሪካ ሞግረኒና ጋርም በጋራ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይታቸው ወቅትም ከሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ከአገራቱ ጋር ለመስራት ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም