ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር ተወያዩ
48
አዲስ አበባ የካቲት 4/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር በአህጉራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረጉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት መሃመድ ፋርማጆ፣ ከጋናው ፕሬዝዳንት ናና አኩፎና ከቦትስዋና ፕሬዝዳንት ሞክግዌሲ ማሲሲ ጋር መክረዋል።
በተጨማሪም ከቱንዝያው ፕሬዝዳንት ቤጂ ካይድ ኢሴብሲ እና ከሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ጋር በቀጠናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
ዛሬ በሚጠናቀቀው 32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ጎን ለጎን ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች መሪዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እየመከሩ ነው።
በትናንትናው እለትም ከሱዳን እና ግብፅ መሪዎች ጋር የሶስትዮሽ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።