ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአውሮፓ ህብረት ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

63

አዲስ አበባ ጥር 30/2011  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የአውሮፓ ህብረት ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኮሚሽነር ኒቨን ሚሚካንን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

በውይይታቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤልጅየም ብራስልስ ይፋዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከአውሮፖ ህብረት ኮሚሽን አመራሮች ጋር ካደረጉት ውይይት የቀጠለ ነው።

በውይይቱ ወቅት ሚሚካ የአውሮፖ ህብረት በኢትዮጵያ ለሚካሄደው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ያለውን ድጋፍ በመግለጽ ህብረቱ የልማት ፕሮጀክቶችን በገንዘብ መደገፍ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ትስስር ህልምን ተመርኩዞ በቀጠናው የሚካሄዱ ጥምር የልማት ፕሮጀክቶችን እንደሚደግፍ መግለፃቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም