ኢትዮጵያና ጊኒ ስትራቴጂክ አጋርነት ለመፍጠር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

490

አዲስ አበባ ጥር 30/2011 ኢትዮጵያና ጊኒ ስትራቴጂክ አጋርነት ለመፍጠር የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁና የጊኒው አቻቸው ማማዲ ቱሬ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተፈራርመዋል።

አገራቱ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን አቋቁመው ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የሚስችል ስምምነትም አድርገዋል።h

ኢትዮጵያና ጊኒ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት፣ጤና፣ባህልና ቱሪዝም ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።

በተለያዩ መስኮች የተደረሱትን ስምምነቶች ከዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በተጨማሪ የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን፣የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ወልደማርያምና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ከጊኒው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማማዲ ቱሬ ጋር ተፈራርመዋል።

የጊኒ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር አልፋ ኮንዴ በኢትዮጵያ ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

ኢትዮጵያና ጊኒ በቀድሞ መሪዎቻቸው በቀዳማዊ ኃይለስላሴ እና በፕሬዝዳንት ሴኩ ቱሬ የቀድሞውን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በግንባር ቀደምትነት የመሰረቱ አገሮች ናቸው።

ጊኒ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1958 በፕሬዝዳንት አህመድ ሴኮ ቱሬ እየተመራች ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነፃ መውጣቷ ይታወሳል።