የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣይ ግንኙነታቸው ዙሪያ እየመከሩ ነው

59

አዲስ አበባ ጥር 29/2011 የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣይ በተናጥልና በጋራ የሚኖራቸውን ግንኙነት የሚገዛ የአሰራር ስርዓት ቃል-ኪዳን ላይ ውይይት እያደረጉ ነው።

ለውይይቱ  ሰባት  የቀጣይ መወያያ አጀንዳዎች ቀርበዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉዳዮች የሚመራበት ደንብና ስርዓት፣ የምርጫ ቦርድ አደረጃጀት፣ የ2012 ዓ.ም ምርጫ፣ አገራዊ መግባባት፣ህገ-መንግስትና ፌዴራሊዝም፣የዴሞክራሲ ተቋማት ማሻሻያና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በቀጣይ የሚወያዩባቸው አጀንዳዎች ናቸው።

እስካሁን ባለው ሄደትም በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚኖረውን ግንኙነትና በተናጥል የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች የሚገዛ የአሰራር ስርዓት ቃል-ኪዳን ሰነድ ላይ በመወያየት ''ይህ ይጨመር'' ''ይህ ይቀነስ'' በማለት ላይ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት በውይይቱ እንዲሳተፉ ጥሪ የተደረገላቸው 103 አገራዊ፣ ክልላዊና በቅርቡ ከውጭ አገራት የመጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም