ኢዜአን እንደገና ለማቋቋም የቀረበው አዋጅ ጸደቀ

1328

አዲስ አበባ ጥር 29/2011 የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበው አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ ጸደቀ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላትና የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች በቅርቡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ራሱን ችሎ እንዲቋቋም በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ ላይ ውይይት ማካሄዳቸው ይታወሳል።

በዛሬው ዕለትም ምክር ቤቱ ባካሄደው ልዩ ስብሰባ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበውን አዋጅ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል።

አዋጁ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ብቁና ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲቀጥልና መረጃ ለመስጠት ተቋማዊ የአሰራር ነፃነት ሊኖረው እንደሚገባ ታምኖበት የተዘጋጀ መሆኑም ተገዕጿል።

በአዋጁ መሠረት ኢዜአ ሙያዊ ብቃቱን ብቻ ሳይሆን ገቢ በሚያስገኙ የተለያዩ ስራዎች ላይ በመሰማራትም የገቢ አቅሙን ያሳድጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከ75 ዓመታት በላይ በአዲስ አበባና እና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ባሉት ከ30 በላይ ቅርንጫፎች ለደንበኞቹ መረጃዎችን በማድረስ የአገሪቱ ዋነኛ የዜና ምንጭ በመሆን እያገለገለ ያለ ተቋም ነው።