ወጣቶች የተጀመረው የለውጥ ጉዞ አንዳይቀለበስ ነቅተው እንዲጠብቁ አክቲቪስት ጃዋር ጠየቀ

67

ሰመራ ጥር 28/2011 ወጣቶች በአገር የተጀመረው የለውጥ ጉዞ አንዳይቀለበስ  ነቅተው እንዲጠብቁ  አክቲቪስት ጃዋር መሐመድ ጠየቀ።

አክቲቪስት ጃዋር ከሰመራና ሎጊያ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ትናንት ተወያይቷል።

አክቲቪስት ጃዋር  በዚሁ ወቅት እንዳለው  ወጣቱ እንደ አገር የተጀመረው ለውጥ ለማደናቀፍ የሚጥሩ አካላትን ነቅተው እንዲጠብቁ አሳስቧል።

ችግሮችን በየደረጃው ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ በመወያየትና በመመካከር መፍታትና ከመንግሥት ጎን እንዲቆሙም  አስገንዝበዋል።

ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ወጣት ከድር ዓሊ እንዳለው ለውጡን አስተማማኝ ደረጃ  ለማድረስ ብዙ ሥራዎች እንደሚቀሩ ተረድቻለሁ ብሏል።

ወጣት ሰዲቅ ሁሴን በበኩሉ የአፋር ወጣቶች ለውጡን ለማምጣት የንብረት ውድመትም ሆነ በሕይወት ላይ ጉዳት ሳይደርስ ትግል ማካሄዳቸውን አስታውሶ፤በክልሉ ሰላም አንዲሰፍንና  የሕዝቦች አንድነትና አብሮነት ለማረጋገጥ ድርሻውን እንደሚወጣ ገልጿል።   

የአፋር ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ  መሐመድ አክቲቪስቱ ሰላማዊ የትግል ስልቶችን በመቀየስና  ወጣቶችን በማታገል ግንባር ቀደም ሚና መጫወቱን መስክረዋል። 

የክልሉ ወጣቶች ከአክቲቪስት ጃዋር የትግል ስልቶች ተሞክሮ በመውሰድ ለውጡን እንደሚያስቀጥሉ እምነታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም