የጊዳቦ ግድብና መስኖ ልማት ፕሮጀክት ተመረቀ

97

አዲስ አበባ ጥር 26/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የጊዳቦ ግድብና መስኖ ልማት ፕሮጀክትን መርቀው ከፈቱ።

በ2002 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው የጊዳቦ ግድብና መስኖ ልማት ፕሮጀክት በሁለት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ቢባልም ከተባለለት ስድስት ዓመት ዘግይቶ ዛሬ ተመርቋል።

ከአዲስ አበባ በ365 ኪሎ ሜትር ርቀት፣ ከዲላ ከተማ አቅራቢያ ጊዳቦ በተሰኘ የደቡብና የኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ቦታ ላይ ነው ግድቡ የተገነባው።

በሁለት ዓመታት ውስጥ ግንባታው እንደሚጠናቀቅ ታቅዶና በ258 ሚሊዮን ብር በጀት የተጀመረው የጊዳቦ ግድብና መስኖ ልማት ፕሮጀክት በ1 ነጥብ 26 ቢሊዮን ብር ተጠናቋል።

ግድቡ ከ63 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውኃ የመያዝ አቅም ሲኖረው 13 ነጥብ 5 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ለማልማት ያስችላልም ተብሏል።

በግድቡ ግራና ቀኝ ዋና ዋና የውኃ ቦዮች መገንባታቸውና በአሁኑ ወቅትም ከ1 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ያካለለ ውኃ በግድቡ መጠራቀሙም ታውቋል።

በምርቃቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ስለሺ በቀለን ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ፣ የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ፣ የሁለቱ አጎራባች ክልሎች ነዋሪዎች፣ አባ ገዳዎችና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም