ባለፉት ስድስት ወራት የግብር አፈጻጸሙ የ8 ነጥብ 6 በመቶ እድገት አሳይቷል

103

አዲስ አበባ ጥር 24/2011 በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት የተሰበሰበወ ግብር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ8 ነጥብ 6 በመቶ እድገት ማሳየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።

ነገር ግን አሁንም ቢሆን መሰብሰብ የሚገባውን ያህል ግብር እየተሰበሰበ አይደለም ብለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት፤ ግብርን በአግባቡ መክፈል ግዴታ መሆኑን በማስገንዘብ ረገድ እንደ አገር አሁንም በርካታ ተግባራት መከናወን  አለባቸው።

ከግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ጎን ለጎን ግብርን የሚመለከቱ ጠንካራ ህጎች እንደሚወጡም አክለዋል።

የአሰባሰብ ስርዓቱን ዘመናዊና ቴክኖሎጂን በመጠቀም ተደራሽ በማድረግ ከግብር የሚገውን ገቢ ለማሳደግ እንደሚሰራም ጠቅላይ ሚንስትሩ ጨምረው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሚገኙ አገራት መካከል ዝቅተኛ ግብርን በመሰብሰብ ስሟ በተደጋጋሚ የሚጠቀስ ሲሆን፤ በቅርቡም ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድና ሌሎች ባለድርሻ አከላት የተሳተፉበት የግብር ንቅናቄ መድረክ መጀመሩ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም