በውጭ አገራት የነበሩ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን እንደግፋለን-የምክር ቤት አባላት

54

አዲስ አበባ ጥር 24/2011 ፓርላማው ብዝሃ-ሀሳብ የሚስተናገድበት እንዲሆን ከውጭ የመጡ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ለመደገፍ መዘጋጀታቸውን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ።

ለረጅም ዓመታት በውጭ አገር ሲታገሉ የነበሩ ከ20 በላይ ተፎካካሪ ፓርቲዎች መንግስት ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ይታወሳል።

ይሁንና ፓርቲዎቹ እስካሁን በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው አጀንዳቸውን ለህዝብ ማስተዋወቅ አልጀመሩም፤ የራሳቸውን ጉባኤም አላካሄዱም።

ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስተያየታቸውን የሰጡት የምክር ቤት አባላት ከውጭ በሰላማዊ መንገድ የገቡ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ወደ ፓርላማ ገብተው የህዝቡ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

ለዚህም  ከልምዳቸው  ለማካፈልና ፓርቲዎቹን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሆኑት አቶ ተስፋዬ ሮበሬ ''የምክር ቤት አባላት ሀሳባቸው ትክክለኛ ከሆነ በትክክለኛ መንገድ ከመጡ ምንም ችግር የለውም ይፈለጋል ምክንያቱም የብዙሃን ድምጽ ለኢትዮያ በጣም ወሳኝ ስለሆነ በአንድ ብቻም ሊሆን አይችልም ህዝቡ አማራጭ ሊኖረው ይገባል።ዓላማውም ከዚያ አኳያ ስለሆነ ይሄ የሚበረታታ ሀሳብ ሀሳብ  ነው።''

''ለእነሱም ለኛም አንድ አገር ናት ይህቺን አገር ለማልማት ከጥፋት ለማዳን ደግሞ ተደጋግፈን የመስራት ሃላፊነት ስላለብን እጅ ለእጅ ተያይዘን ለመስራት ዝግጁ ነን እነሱም ደግሞ  መዘጋጀት አለባቸው'' ያሉት አባል ወይዘሮ ማርታ ረኪሱ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም