የጀርመኑ ፕሬዚዳንት የአፍሪካ ህብረትን ጎበኙ

125

አዲስ አበባ ጥር 22/2011 የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴይንሜዬር የአፍሪካ ህብረትን ጎበኙ ።

ፕሬዚዳንቱ ከህብረቱ ምክትል ኮሚሽነር ኩዋዚ ኳርቲ እና ከሌሎች የስራ ሃላፊዎች ጋር ዝግ ውይይት አካሂደዋል።

ፕሬዚዳንቱ በሰላምና በደህንነት ጉዳዮች ዙሪያና የውጭና የደህንነት ፖሊሲ በሚጠናከርበት ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ለማወቅ ተችሏል።

በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴይንሜዬር ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር በሁለትዮሽ ትብብር ላይ መምከራቸው የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም