ስሑል ሽረ ደደቢትን አንድ ለባዶ ሲያሸንፍ፤ወላይታ ዲቻና ባህር ዳር ከነማ አቻ ወጡ

85

መቀሌ ጥር 20/2011 በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የ13ኛ ሳምንት ጨዋታ ስሑል ሽረ ደደቢትን አንድ ለባዶ አሸነፈ።

በወላይታ ሶዶ ከተማ የተገናኙት ወላይታ ዲቻና ባህር ዳር ከተማ አንድ ለአንድ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ስሑል ሽረ  ተጋጣሚውን ያሸነፈው ሰይድ ሁሴን በ80ኛው ደቂቃ ባገባት ብቸኛ ግብ ነው።

ከለቡ በመቐለ በትግራይ ስታዲዬም በተካሄደው ግጥሚያ ያከማቸውን ነጥብ ወደ 12 ከፍ አድርጓል። 

በአንጻሩ ደደቢት በ13 ውድድሮች አራት ነጥብ  በመያዝ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የሰሑል ሽረ ክለብ ምክትል አሰልጣኝ ገብረኪሮስ አማረ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት ከዕረፍት በኋላ የተሻለ እንቅስቃሴና የተጫዋች ቅያሪ በማድረግ አሸንፈው መውጣታቸውን ተናግረዋል።

በቀጣይ በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች በጥሩ ሥነ ልቡና ተጠናክረው በመግባት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንጥራለን ብለዋል።

የደደቢት ክለብ አሰልጣኝ ኤልያስ ሐሰን በበበኩላቸው ክለባቸው ከዕረፍት በፊት ጥሩ ተጫውቶ ያገኘናቸው ዕድሎች እንዳልተጠቀመበት ገልጸዋል።ከዕረፍት መልስ ግን ጨዋታቸው በመቀዛቀዙ ግብ ለማስተናገድ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲዬም የተገናኙት ወላይታ ዲቻና ባህር ዳር ከነማ አንድ አቻ ወጥተዋል።

ክለቦቹ አቻ የሚያደርጓቸው ግቦች ያስቆጠሩት በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡

ለወላይታ ዲቻ ግቧን በ17ኛው ደቂቃ በባዬ ገዛኸኝ  ሲያስቆጥር፤ ለባህር ዳር ከነማ ደግሞ በ44ኛዉው ደቂቃ ጃኮ አራፋት አቻ የምታደርገውን ግብ አስገብቷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም