የምስራቅ ወለጋ ዞን ከተሞች እግር ኳስ ውድድር በበረዳ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የምስራቅ ወለጋ ዞን ከተሞች እግር ኳስ ውድድር በበረዳ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
65
ነቀምቴ ግንቦት 19/2010 ለአንድ ሳምንት ሲካሄድ የቆየው የምስራቅ ወለጋ ዞን ከተሞች እግር ኳስ ውድድር በበረዳ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ያደታ ጭምዴሳ በመዝጊያ ስነስርዓት ወቅት እንደተናገሩት፤ የውድድሩ ዓላማ በከተሞች መካከል የመቀራራብ እና የመቻቻል ባህል ለማዳበር ነው፡፡ እንዲሁም በአሮሚያ በሚደረገው ሻምፒዮን ላይ ዞኑን ወክለው የሚሰለፉ ስፖርተኞች ለመመልመል ጭምር እንደሆነም አመልከተዋል፡፡ በውድድሩ የበረዳ ከተማ አስተዳደር፣ የገባ ጅማታ እና አንገር ጉቴ ከተሞች ከአንደኛ አስከ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ እንደቅደም ተከተላቸው የወርቅ፣የብርና የነሓስ ሜዳሊያ ተበርክቶላቸዋልል። ለውድድሩ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ መስሪያ ቤቶች፣ ዳኞችና ሌሎችም አካላት የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል። ለአንገር ጉቴ ከተማ ከነሓስ በተጨማሪ የጸባይ ዋንጫም ተሸላሚ ሆነዋል።