የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ተካሄደዋል - ኢዜአ አማርኛ
የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ተካሄደዋል
60
አዲስ አበባ ጥር 20/2011 የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ተካሄደዋል።
ትናንት በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም መከላከያ በሊጉ አዲስ ተሳታፊ የሆነውን ጎንደር ከተማ 35 ለ 20 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በክልል ከተማ ቡታጅራ ላይ ከምባታ ዱራሜ ቡታጅራ ከተማን 25 ለ 13 ረቷል።
ከትናንት በስቲያ በፕሪሚየር ሊጉ ሶስት ጨዋታዎች ተካሄደዋል።
በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም የአምናው የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፌዴራል ማረሚያ ቤቶችን 28 ለ 24፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ፌዴራል ፖሊስን 32 ለ 26 አሸንፈዋል።
ድሬዳዋ ላይ መቐለ ሰብዓ እንደርታ ድሬዳዋ ከተማን 22 ለ 15 ማሸነፍ ችሏል።
በኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ 10 የእጅ ኳስ ቡድኖች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።