የትግራይ ክልል ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ተጀመረ

62

መቀሌ ጥር 16/2011 ምክር ቤቱ ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቆየውን ጉባኤውን የጀመረው የግማሽ ዓመት የስራ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን በማዳመጥ ነው።

የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የክልሉን የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን በማቅረብ ላይ ናቸው።

ምክር ቤቱ በአራት ቀናት ቆይታው የምክትል ርእሰ መስተዳድሩን ሪፖርት ተወያይቶ ከማጽደቅ በተጨማሪም የዋና ኦዲተርና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሪፖርት ላይ ይወያያል።

በክልሉ ንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ስር በስራ ሂደት ደረጃ ላይ የነበረው የክልሉ የኢንቨስትመንት ጽህፈት ቤት በኮሚሽን ደረጃ እንዲቋቋም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በተመሳሳይም በፍትህ ቢሮ ስር በስራ ሂደት ደረጃ ተዋቅሮ የነበረው የክልሉ የወሳኝ ኩነት ጽሕፈት ቤትም የተሻለ ስራ እንዲያከናወን ለማስቻል ወደ ኤጀንሲ ደረጃ እንዲያድግ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅም ያጸድቃል።

በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ስራ ላይ እንዲውል በተደረገው የማንነትና የወሰን ማስከበር ኮሚሽን አዋጅ ላይ በመወያየትም የአቋም ውሳኔ እንደሚሰጥበት ከጉባኤው የዝግጅት መርሃ-ግብር ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም