የሶማሌ ክልል መንግሥት ስድስት ከፍተኛ አመራሮቹን ከኃላፊነት አነሳ

876

ጅግጅጋ  ጥር 15/2011 የሶማሌ ክልል መንግሥት ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ አንድ የካቢኔ አባልን ጨምሮ ስድስት ከፍተኛ አመራሮችን ከኃላፊነታቸው አነሳ።

ካቢኔው ከኃላፊነት ካነሳቸው መካከል የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ፣የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኃላፊና የምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አማካሪ ይገኙበታል።

በክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጉሌድ ቦታም ቢሮውን በምክትል ቢሮ ኃላፊነት ደረጃ ሲመሩ በነበሩት በአቶ አብዱላሂ መሐመድ ተተክቷል።

የክልሉን ገዢ ፓርቲ የሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ሶሕዴፓ)ንና የክልሉን መንግሥት አስመልክቶ በማህበራዊ ድረ-ገጾች የሚናፈሰው ወሬ መሠረተ ቢስ መሆኑን አቶ አብዱላሂ መሐመድ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ገልጸዋል።