እንግሊዝ ከህብረቱ የመነጠል መብትን በተመለከተ የሚደነግገው አንቀፅ 50 መራዘሙን ተቃወመች

95

አዲስ አበባ ጥር 14 / 2011 የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ አገራቸው የአውሮፓ ህብረት የአባል አገራቱ ከህብረቱ የመነጠል መብትን በተመለከተ የሚደነግገው አንቀፅ 50 ማሻሻያ ሃሳብ ሳይታቀድና በቂ ምክክር ሳይደረግበት ማራዘሙ አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ ገልፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ሃገራቸው ከአውሮፓ ህብረት ጋር እንድትቆይ የተደረገላቸውን ጥሪንም እንደማይቀበሉ  አሳውቀዋል

እንግሊዝ የ 28  አባል ሃገራት ስብስብ ከሆነው የአውሮፓ ህብረት የመነጠል እንቅስቃሴ የተጀመረችው ከሁለት አመት በፊት  መጋቢታ 29 / 2016 ሲሆን አባል ሃገራት ከህብረቱ መነጠል ሲፈልጉ ማሟላት ያለባቸውን  መስፈርት  በተመለከተ የሚደነግገው አነቀፅ 50ን  መሰረት በማድረግ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትሯ   የአንቀፅ 50 ያለ ስምምነትና በቂ ምክኒያት  መራዘምን  እንደማይቀበሉና አግባብነት እንዴሌለው አሳስበው ሃገራቸው ከህብረቱ ፍች የምትፈፀምበት ሌሎች በርካታ አማረጮች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡

"ነገር ግን ይህ ሲሆን  ትክክለኛውን መንገድ መነጠሉን በተመለከተ ማንኛውንም የመንግስት  የስራ እንቅስቃሴ  ለህዝባችን ማሳወቅ  ይጠበቅብናል" ብለዋል

የመጀመሪያው አማራጭ ከኅብረቱ መነጠልን በተመለከተ የሚደነግገውን አንቀፅ 50 በአጭር ጊዜ ተግባራዊ እንዲሆን  ማድረግ ፣ሁለተኛው ደግሞ ከአንቀፁ ውጭ ያሉ አማረጮችን መጠቀም፣ ይህ ማለት ግን እንደ አማራጭ መንገድ እንጅ ህግን እንደ መጣስ መቆጠር እንደሌለበት አስገንዝበዋል፡፡

የእንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት ጋር አብሮ መቀጠል አገራቸውን በኢኮኖሚው ዘርፍ ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍላትና አሁንም እያስከፈላት እነደሚገኝ ቴሬዛ ሜይ ፓርላማ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል፡፡

 በእንግሊዝ ከ 3 ሚሊዮን በላይ የአባል ሃገራቱ ዜጎች እንደሚኖሩ ገልፀው በቀጣይም እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት ስትወጣ ከተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት የሚመጡና  ከዚህ በፊት በሃገሪቱ የሚኖሩ ዜጎች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተለየ ሁኔታ የኦላይን ምዝገባና የ  65 ዩሮ ክፍያ እንደሚጀመር አስታውቀዋል፡፡

የኢንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት የመነጠል ጉዳይን በተመለከተ ድጋሜ ህዝበ ውሳኔ እንደማይካሄድ አክለው ገልፀዋል፡፡

የኢንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት መነጠልን የሚደግፉ አካላት  የአንቀፅ 50 ምክክርና ድርድር ሳየደረግበት መራዘም አግባብነት እንደሌለው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የአውሮፓ ህበረት የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር ፣ የጋራ የኢኮኖሚ ቀጠና ለመፍጠር፣ በሰላም ዙሪያ በጋራ ለመስትና በአጠቃላይ አውሮፓን ለመቀየር እ.አ.አ በ1945 እንደተመሰረተ ይታወቃል፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም