በሳሲጋ ወረዳ የእርቀሰላም ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው

56

ነቀምቴ ጥር 14/2011 በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት የሚያግዝ የእርቀሰላም ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው።

ኮንፍረንሱ ከዛሬ ጀምሮ እየተካሄደ ያለው በምስራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ ሀድረ በሎ ቀበሌ ውስጥ መሆኑ ታውቋል።

በካማሺ ዞን አዋሳኝ አካባቢ እየተካሄደ በሚገኘው ኮንፍረንስ  አባገዳዎች፣ የኃይማኖት አባቶች ፣የሀገር ሽማግሌዎች፣  የዞንና የወረዳ አመራሮች እየተሳተፉ ናቸው፡፡

የእርቀ ሰላሙ ኮንፍረንስ ሂደት ዝርዝር መረጃ በስፍራው የሚገኘው ሪፖርተራችን እንዳደረሰን እናቀርባለን፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም