የአንታርቲካ በረዶ መቅለጥ ስጋት እየሆነ ነው

1595

ጥር 8/2011በቅርቡ በአንታርቲካ  ጥናት ያካሄደው የአሜሪካ ብሄራዊ አካዳሚ ሳይንስ ተቋም  እ.አ.አ ከ 1979 ጀምሮ ለአለፉት 40 አመታት  በአካባቢው የበረዶ መቅለጥ በየ አመቱ በ 6 እጥፍ እየጨመረ  መምጣቱን ገልጿል፡፡

ተቋሙ የአለማችን የሙቀት መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መምጣትን   በምክንያትነት  ጠቅሶ ከ 1979-2017 ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ የባህር ጠለል በ 1.4 ሴንቲ ሜትር ከፍ እያለ መምጣቱን  በሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

 ተመራማሪዎቹ  በቅርቡ በ 18 የአንታረቲካ ቦታዎች በመርከብ በመዘዋዎር ባካሄዱት ጥናት በአካባቢው በየጊዜው የበረዶ መቅለጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን አረጋግጠዋል፡፡

የአንታርቲካ የበረዶ መቅለጥ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ  በቀጣይ ጥቂት አመታት  ውስጥ የባህር ጠለል መጠን በከፍኛ መጠን እንደሚጨምርና በአለም ላይ ለሚኖሩ የሰው ልጆችም   ዋነኛው የአደጋ ምንጭ ሊሆን እንደሚችል  ስጋታቸውን ጨምረው አስቀምጠዋል፡፡

በዚህ መሰረት ተመራማሪዎች ከ 1979-1990 ድረስ የአንታርቲካ የበረዶ ግግር በየአመቱ በአማካኝ 40 ቢሊዮን ቶን እንደሚቀንስም አረጋግጧዋል፡፡

ከ 2009 ወዲህ  ለአለፉት  አመታት ከነበረው  6 እጥፍ በላይ   በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መምጣቱም ተረጋግጧል።

ሌላው በዘርፉ ጥናት የአካሄደው የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት ተቋም (ናሳ) በበኩሉ   የሳተላይት አሰሳዎችንና የአውሮፕላን ቅኝቶችን በማድረግ  የተለያዩ  ፎቶ-ግራፎችንና መረጃዎችን በማሰባሰብ የሁኔታውን አሳሳቢነት በመጠቆም፤  በቀጣይም  የአለምን የአየር ንብረትን በማስተካከልና  የበረዶ  መቅለጥን በመቀነስ ረገድ ሰፊ ስራ መሰራት እንዳለበት ጠቁሟል፡፡

ከዚህ ቀደም በመስኩ የተካሄዱ ጥናቶች ወደ ፊት እ.አ.አ በ 2100 በባህር ዳርቻ አካባቢ የሚገኙ ከተሞች ቅድመ ጥንቃቄ ካልተድገላቸው  በጎርፍ እንደሚጠቁና ብዙ ነዋሪዎችንም ከመኖሪያ ቀያቸው ሊያፈናቅል እንደሚችል ሰጋታቸውን ማስቀመጣቸው   ይታወሳል፡፡   

ምንጭ፡አልጄዚራ