ብሪታኒያ ከአውሮፓ ህብረት ለመውጣት የደረሰችው ስምምነት ውድቅ ሆነ

51

ጥር 8/2011 ብሪታኒያ ከአውሮፓ ህብረት ለመውጣት የደረሰችው ስምምነት በሀገሪቱ ምክር ቤት በከፍተኛ ተቃውሞ ውድቅ ሆነ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ ሀገራቸውን ከአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመነጠል የደረሱት ስምምነት በህግ አውጭው ምክር ቤት አባላት በአብላጫ ድምፅ ውድቅ ሆኗል።
ስምምነቱ በምክር ቤቱ ድምፅ ተሰጥቶበት 432 አባላት ሲቃወሙት 202 ብቻ ደግፈውታል።
የቴሬዛሜይ እቅድ በምክር ቤቱ ከፍተኛ ተቃውሞ ማስተናገዱን ተከትሎ የተቃዋሚው ሌበር ፓርቲ መሪ ጄሬሚ ኮርቤይን በጠቅላይ ሚኒስትሯ መንግሥት ላይ የመተማመኛ ድምፅ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።
ብሪታኒያ ከአውሮፓ ህብረት ለመነጠል በፈረንጆቹ 2016 ህዝበ ውሳኔ ያካሄደች ሲሆን 52 በመቶ ብሪታንያውያን ሀሳቡን ሲደግፉት 48 በመቶወቹ መቃወማቸው ይታወሳል።
ከብሪታኒያ የመውጣት የስምምነት ምዕራፉ በምክር ቤቱ ውድቅ መሆኑ በሀገሪቱ ፖለቲካዊ ቀውስን ሊያስከትል እንደሚችል ተንታኞች እየገለጹ ነው።
ብሪታኒያ ከመጪው የፈረንጅቹ መጋቢት 29 ቀን በኋላ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ፍቺ እንደምትፈፅም ቀነ ገደብ ቢቀመጥም ሁኔታዎች ተለዋዋጭ እየሆኑ መጥተዋል።
ምንጭ፦ሮይተርስ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም