የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

952

ጥር 8/2011 የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል።

ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የድርጅትና የመንግስት የስራ አፈጻጸም እንዲሁም በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ላይ ሲሆን አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈጻጸምም ይገመግማልም ተብሏል፡፡

በስብሰባው በመስከረም ወር በሀዋሳ በተካሄደው በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የአጋር ፓርቲዎች ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን ከኢህአዴግ ፅ/ቤት የተገኘ መረጃ ያሳያል።