የጊዳቦ የመስኖ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቀቀ

111

ጥር 7 /2011 ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የጊዳቦ የመስኖ ፕሮጀክት በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚመረቅ የውሃ ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የመስኖ ግድቡ በኦሮሚያና በደቡብ ክልል መሃከል የሚገኝ ሲሆን 62.5 ሚሊየን ሜትሪክ ኪዩቢክ ውሃ የመያዝ አቅምና 13 ሺህ 425 ሄክታር መሬት ያለማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው የመስኖ ግድቡ 10ሺህ አርሶ አደሮች ይጠቀሙበታል፤ ለ 192 ሺህ ወጣቶችም የስራ እድል ይፈጥራል፡፡

ግንባታው ስምንት አመታት የፈጀ ሲሆን የግንባታ ዲዛይን መቀየሩ ለመዘግየቱ ምክንያት  ሆኗል ተብሏል፡፡

የኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽንና የኮንስትራክሽን ስራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን በማማከሩ ስራ እንደተሳተፉበት ተገልጿል፡፡

የመስኖ ግድቡ 25.8 ሜትር ቁመትና 335 ሜትር እርዝመት አለው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም