ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ መከሩ

82

አዲስ አበባ ጥር 6/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማቡዛን ተቀብለው አነጋገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክትል ፕሬዝዳንቱ ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው በተወያዩበት ወቅት የሁለቱ አገሮች ታሪካዊ ግንኙነት በሚጠናከርበት ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርገዋል።

በቅርቡ በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ህብረት አስቸኳይ የመሪዎች  ስብሰባ የተገኙት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በሁለቱ አገሮች ግንኙነትና ትብብር ዙሪያ መምከራቸው ይታወሳል።

የደቡብ አፍሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ማቡዛ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነትና ትብብር ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም