ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ባህርዳር ገቡ

80

ባህርዳር ጥር 6/2011 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ዛሬ ባህርዳር ሲገቡ አቀባበል ተደረገላቸው።

በአቀባበል ስነ-ስርዓት ወቅት የባህርዳር ሀገረስብከት ሊቀ ጰጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ አብርሃም  " ቅዱስ አባታችን ከ27 ዓመት የስደት ቆይታ በኋላ ለሃገራቸው በቅተዋል" ብለዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ከስደት በክብር ወደሃገራቸው  መመለስ በመቻላቸው ለህዝበ ክርስቲያኑ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ መምሪያ ኃላፊ ሊቀ ማይምራን ፈንታሁን ሙጬ በበኩላቸው  "ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ከስደት ሀገር ተመልሰው እናንተን ለመባረክ  እንኳን አበቃችሁ" ብለዋል።

በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ የዕምነቱ ተከታዮች፣ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ቀሳውስት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራንና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም