ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ሽሬ እንዳስላሴ ገቡ

108

ሽሬ እንዳስላሴ ጥር 6/2011 ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ሽሬ እንዳስላሴ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

ቀዳማዊት እመቤቷ ዛሬ ረፋድ ላይ ሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ሲገቡ የክልሉ ምክትል ርእሰ-መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የከተማው ነዋሪ ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

ወይዘሮ ዝናሽ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ለሚገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሰረተ ድንጋይ ያስቀምጣሉ ተብሎም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም