በግልገል በለስ ከተማ 3 ሺህ 500 ነዋሪዎች የተሳተፉበት የእርምጃ ውድድር ተካሄደ

107

አሶሳ ጥር 5/2011 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግልገልበለስ ከተማ 3 ሺህ 500 ነዋሪዎች የተሳተፉበት የእርምጃ ውድድር ዛሬ ተካሄደ፡፡

የኅብረተሰቡን ጤና በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለመጠበቅ ዓላማው ባደረገው ይህው  ውድድር የአምስት ኪሎ ሜትር የሚሆን ሲሆን የከተማውና አካባቢው ነዋሪዎች መሳተፋቸውን የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ትዕዛዙ ታዬ ገልጸዋል፡፡

''የኅብረተሰቡ የስፖርት ተሳትፎ ለላቀ ጤንነት!'' በሚል መሪ ቃል የተደረገውን ውድድር ቀድመው ያጠናቀቁ አንድ ሺህ ሰዎች ሰርተፊኬት አግኝተዋል ብለዋል፡፡

የከተማው አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጊሳ ዘሪሁን በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኅብረተሰቡ በማናቸውም የሥራ አካባቢ እንቅስቃሴ በማድረግ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ራሱን ሊጠብቅ ይገባል፡፡

አስተዳደሩ ውድድሮችን ቀጣይ በማድረግ ከክልሉ መንግሥት ጋር እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

የከተማው በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ውድድሩ በሠላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ  እገዛ ማድረጋቸው ተመልክቷል፡፡

ውድድሩን ያዘጋጁትየፌደራልና የክልሉ ስፖርት ኮሚሽኖች ከመተክል ዞን ስፖርት ምክር ቤት ጋር በመተባበር ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም