ኢትዮጵያና ሴራሊዮን ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

65

አዲስ አበባ ጥር 5/2011 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሴራሊዮኑ ፕሬዝዳንት ጁልየስ ማዳቢዩ ጋር የሁለቱን አገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገድ ላይ መከሩ።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን በሴራሊዮን የሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ነው።

የልኡካን ቡድኑ የማዕድን ሚኒስትር እና የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽነርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትን ያካተተ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ፅሀፈት ቤት አስታውቋል። 

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትናንት በስተያ ፍሪታውን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ጁልየስ ማዳቢዩ ጋር የሁለቱን አገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገድ ላይ ተነጋግረዋል።

መሪዎቹ በተለይም በማዕድን፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በቱሪዝም እና በሌሎች ዘርፎች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

አገራቱ ያካሄዱትን የሁለትዮሽ ውይይት ተከትሎ በመካከላቸው በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ሁለት ስምምነቶችን ፈርመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም