በሀረቀሎ ከተማ በግለሰብ ቤት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ

180

ነገሌ ጥር 4/2011 በጉጂ ዞን ሀረቀሎ ከተማ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ ተከማችተው የተገኙ  ህገወጥ  የጦር መሳሪያዎች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

በዞኑ የጎሮዶላ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አስቻለው ደበበ ለኢዜአ እንደገለፁት ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ትላንት ቀን  ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የጦር መሳሪያዎቹን ሊይዝ ችሏል።

በፍተሻ የተያዙት እነዚህ  የጦር መሳሪያዎች አምሰት ቸኮዝ፣አንድ ዴሞትፎርና አንድ ምንሽር ጠመንጃዎች መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የተያዙት የጦር መሳሪዎች አከማችቷል ተብሎ የተጠረጠረው  ግለሰብ ለጊዜው በመሰወሩ ፖሊስ ክትተል እያደረገበት መሆኑን ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል ።

ወረዳው የጦር መሳሪያ ዝውውር የሚካሄድበት በመሆኑ ህብረተሰቡ የጀመረውን ህገ ወጥ ድርጊት  የማጋለጥ ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።