የግብር ስወራ መንግስትን ብድርና እርዳታ ላይ እንዲያተኩር አድርጎታል

365

አዲስ አበባ በጥር 3/2011 በኢትዮጵያ የግብር ስወራ መንግስት ብድርና እርዳታ ላይ እንዲያተኩር ጫና መፍጠሩን ገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ።

የግብር ስወራ ድርጊትን ለማስቀረት የግብር አሰባሰብ ስርአቱን ማዘመንና ቁጥጥርን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

በሚኒስቴሩ የታክስ ማጭበርበር ምርመራ ዳሬክተር አቶ ሲሳይ ገዙ እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ግብር የመክፈል ባህል ባለማደጉ ከፍተኛ የታክስ ስወራ አለ።

በዚህም ባለፉት አመታት ግብር ከፋዮች ሃሰተኛ ደረሰኝ በማቅረብ፣ ገቢን አሳንሶ በማሳወቅ፣ ኪሳራን በማስመዝገብና ሌሎች የማጭበርበሪያ ስልቶችን በመጠቀም አገር ማግኘት ያለባትን ገቢ አጥታለች።

በ2010 ዓ.ም ብቻ ከ124 በላይ ድርጅቶች በሃሰተኛ ማንነትና ትክክለኛ ባልሆነ ደረሰኝ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት ፈጽመዋል።

መሰብሰብ ያለበት ገቢ ባለመሰብሰቡ ለልማት ስራዎች መንግስት ብድርና እርዳታን እንደ አማራጭ እንዲጠቀም ያስገደደው መሆኑን ተናግረዋል።

ችግሩን ለመቀነስ ግብር ከፋዮች እቃውን ስለመግዛታቸው ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ የመከታታያ ስልት ተቋሙ መዘርጋቱን ይናገራሉ።

የግዥ ልውውጡ በጥሬ ገንዘብ መሆኑ ሌላው ማጭበርበር የሚፈጸምበት በመሆኑ እዚህ ላይም ገደብ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ጨምረዋል።

በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ መምህርና የግብር ተመራማሪ ዶክተር አዝሚ አደም ሃሰን የአገር ውስጥ ገቢ ተቋማት ጠንካራ አለመሆን፣ አሰራሮችን አለማዘመን፣ ግብር ከፋዩ የሚያጋጥሙትን ችግሮች አለመለየትና ሌሎችን ለግብር መሰወር በምክንያትነት ያስቀምጣሉ።

በተጨማሪም ግብር የሚያጭበረብሩ ግብር ከፋዮችን መለየትና ግብር ሰብሳቢ ተቋማትን ማጠናከር በመፍትሄነት ያቀርባሉ

አሁን ያለውን የግብር ስወራ ለመቀነስ የተጨማሪ እሴት ታክስ አሰባሰብ ዘዴን ማጠናከር እንደሚገባ ጥናት ጠቅሰው ይናገራሉ።

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች በበኩላቸው ችግሩን ለመቅረፍ የግብር አሰባሰብ ስርአቱን ማዘመንና ቁጥጥርን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አስተያየት ሰጥተዋል።

“ግብር መሰወር መዋረድ ነው” የሚል አቋም ያላቸው የማራቶን ሞተር ኢንጅነሪንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መልካሙ አሰፋ ግብር በመክፈላቸው ኩራት እንደሚሰማቸው በመግለጽ የግብር ስወራ ድርጊትን ለመቀነስ ግብር ሰብሳቢ ተቋሙ ዘመናዊ አሰራሮችን እንዲከተል መክረዋል።

የበላይ አብ ሞተርስ ማኔጂንግ ዳሬክተር አቶ ፈቃዱ ግርማ ”አንዱ በትክክል እየከፈለ አንዱ የሚሰውርበት አካሄድን መከላከል ካልተቻለ ሌላውም እንዳይከፍል ያደርጋል” የሚል ሃሳብ ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ ግብር ላለመክፈል በተለያየ መንገድ ጥረት እንደሚደረግ ይታወቃል።

በተለይም ከቀረጥ ነጻ አሰራርን እንደአንድ የማጭበርበሪያ መንገድ በመጠቀም አገሪቱ ማግኘት የነበረባትን በቢሊዮን የሚቆጠር ብር እንድታጣ አድርጓል።

ለገቢ አፈጻጸም እየቀነሰ መምጣት ከተለዩ ችሮች ውስጥ የህግ ተገዥነት ባህል የዳበረ አለመሆንና የማጭበርበር ዝንባሌዎች አንዱ ነው።

ግብር የደመወዝ ገቢ ግብር፣ የትርፍ ንግድ ገቢ ግብር፣ ከአክሲዮን የሚከፈል ገቢ የሚጠቀስ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የደሞዝ ገቢ ግብር በትክክል የሚከፈል ሲሆን የትርፍ ገቢ ደግሞ ዝቅተኛ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

የገቢ ግብርን ለማሳደግ የገቢዎች ሚኒስቴር በአሁኑ ወቅት አገራዊ ንቅናቄ ይፋ አድርጎ ከተለያዩ አካላት ጋር እየሰራ ይገኛል።