የኢትዮጵያ ቮሊቦልና እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ይካሄዳል

208

አዲስ አበባ ጥር 3/2011 የኢትዮጵያ የ2011 ዓ.ም ሐበሻ ሲሚንቶ የወንዶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ጨዋታ ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ይካሄዳል።

በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም አዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ከመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከቀኑ 8 ሰዓት ከ30 የሚጫወቱ ሲሆን ወላይታ ድቻ በሜዳው አዲስ አበባ ፖሊስን ከቀኑ 8 ሰአት ላይ ያስተናግዳል ።

እሁድ በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም መከላከያ ከሙገር ሲሚንቶ ከረፋዱ አራት ሰአት ይጫወታሉ።

ጣና ባህርዳር በሜዳው ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ጋር ከጠዋቱ  ሰአት ላይ ይጫወታል።

በሐበሻ ሲሚንቶ የወንዶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ስምንት የቮሊቦል ቡድኖች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ይካሄዳል።

ቅዳሜ በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም የአምና አሸናፊው ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ ከጠዋቱ 3 ሰዓት መከላከያ ከኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከረፋዱ አራት ሰአት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የሊጉ አዲስ ተሳታፊ የሆነው ጎንደር ከተማ በሜዳው ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ከረፉዱ አራት ሰዓት ላይ ይጫወታል።

እሁድ በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም ፌዴራል ፖሊስ ከከምባታ ዱራሜ ከጠዋቱ ሶስት ሰአት በክልል ከተማ መቐለ ላይ መቐለ ሰብዓ እንደርታ ከቡታጅራ ከተማ ከረፋዱ አራት ሰአት ላይ የሚጫወቱ ይሆናል።

በኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ 10 የእጅ ኳስ ቡድኖች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።