የትግራይ ክልል ዓመታዊ የቢስክሌት ሻምፒዮና ቀጥሏል

60

መቀሌ ጥር 2/2011የትግራይ ክልል ዓመታዊ የቢስክሌት ሻምፒዮና በሴቶች የ‘’ቢ’’ ኮርስና በወንዶች ማውንቴን ውድድሮች ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡

ከስድስት ክለቦች የተውጣጡ 95 ቢስክሌተኞች ከመቀሌ- አጉላዕና ዴስአ መስመር 70 ኪሎ ሜትር የሸፈነ የደርሶ መልስ ውድድር አድርገዋል፡፡

የክልሉ ብስክሌት ፌዴሬሸን አልቢትር ፀሃየ አደም ለኢዜአ እንደተናገሩት በውድድሩ ሴት ተወዳዳሪዎች በሰዓት 32 ኪሎ ሜትር፣ወንድ ተወዳዳሪዎች ደግሞ በሰዓት 36 ኪሎ ሜትር ተጉዘዋል፡፡

በሴቶች የ ’’ቢ’’ ኮርስ የቢስክሌት ተወዳዳሪዎች ባደረጉት የደርሶ መልስ ፉክክር ከመቀሌ 70 እንደርታ ክለብ  ሱዛና ተወልደ፣ገነት መኮንንና ማህሌት ፍስሃ በቅደም ተከተል ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ወጥተዋል፡፡

በቡድን ደግሞ መቐለ 70 እንደርታ አንደኛ ደረጃ ሲይዝ ፤መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነዋል፡፡

በወንዶች ማውንቴን ውድድር ከዓዲግራት መጠጥ ውሃ አገልግሎት ግርማአለም አረጋዊና ዕቁባይ ኃይለ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃዎችን ሲይዙ፣  ዮሐንስ ወልዳይ ከመቐለ መጠጥ ውሀ አገልግሎት ሶስተኛ በመሆን አጠናቋል፡፡

በቡድን ደረጃ ደግሞ ዓዲግራት መጠጥ ውሃ አገልግሎት፣ደስታ አልኮልና መጠጥ፣ መቐለ የመጠጥ ውሀ  አገልግሎት በቅደም ተከተል ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

ሁለቱም ጾታዎች የሚካሄደው ሻምፒዮና እስከ ጥር 9 ድረስ ይቀጥላል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም