አቃቤ ህግ በሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ላይ ክስ መሠረተ

54

አዲስ አበባ ጥር 2/2011 አቃቤ ህግ በሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው እና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መሠረተ።

በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት የቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በመዝገብ ቁጥር 229396 ዛሬ በአቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶባቸዋል።

ከእርሳቸው በተጨማሪ በተመሳሳይ ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ረመዳን ሙሳ፣ ኮሎኔል ደሴ ዘለቀ፣ አቶ ቸርነት ዳና ላይ ክስ መመስረቱን አቃቤ ህግ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት አስታውቋል።

በዚህም መሠረት ተጠርጣሪዎቹ በ10ኛ ወንጀል ችሎት የነበራቸው መዝገብ ተዘግቶ ጉዳያቸው በ15ኛ ወንጀል ችሎት እንዲታይ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም